ጋዜጠኞችና ደራሲያን ዕውቅና ሊሰጣቸው ነው
ቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን “ክብር” የተሰኘ የደራሲያንና የጋዜጠኞች ሽልማት ዕውን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
ቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በደራሲና ጋዜጠኛ ቃል ኪዳን ኃይሉ በ2015 ዓም ተመስርቶ “ክብር ሽልማት” ለማዘጋጀት አስር የቦርድ አባላትን አዋቅሮ የተጀመረ ድርጅት ነው።
አበረ አዳሙ ( የደራስያን ማኅበር ፕሬዝዳንት)፣ አቶ አገኘሁ አዳነ ( በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአለ ሥነ ጥበብና ሥነ ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር) ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ( ሰአሊና ቀራጺ)፣ አቶ ጥበቡ በለጠ ( የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት)፣ ዶ/ ር ተሻገር ሽፈራው (፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህር)፣ ዮናስ ሐጎስ ( ጋዜጠኛ)፣ አዳነች ወ/ ገብርኤል ( አርቲስት)፣ ሰለሞን አለሙ ፈለቀ ( ደራሲና አዘጋጅ) እና ቶማስ በየነ ( አርቲስት) የቦርድ አባል አድርጎ በማዋቀር ለደራስያንና ለጋዜጠኞች ውድድር አድርጎ በመጪው ግንቦት ወር ውስጥ ሽልማት ሊሰጥ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
በመሆኑም ሐሙስ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4-5 ሰዓት የሽልማቱ ዋና አዘጋጅ ቃልኪዳን ኃይሉና የቦርድ አባላት በተገኙበት መስቀል አደባባይ በሚገኘው ግሮቭጋርደን የውድድር ሁኔታውንና የሽልማት ሥነሥርአቱን የምንገልጽበት እና ውድድሩን የሚጀመርበት ዕለት መሆኑን የውድድሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡
Website: https://eventaddis.com/
Telegram: https://t.me/EventAddis1