የአንጋፋዋ ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ “ደርሷል ሰዓቱ” የተሰኘ አዲስ ሙዚቃ ከአስር ዓመት በኃላ ዛሬ ሚያዝያ 18 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በቻቺ ታደስ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ተለቋል።
የአንጋፋዋ የበጎፈቃድና የሰላም አምባሳደር ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ “ሰማያችን ሊጠራ ጉም ተኖ ከአድማስ ማዶ እየተፍለቀለቀች እንደምትወጣ የፈካች ውብ ጸሀይ ልትወጣ ይሄው “ደርሷል ሰዓቱ ” ምርታችን ሊያብብ አዝመራችን ሊያጠግበን ሰላማችን ሊበዛ ይሄው “ደርሷል ሰዓቱ” እንድንል የሚያስችለን ብሩህ ዘመን ለሁላችንም እንዲመጣልን ሁላችንም ለሰላምና ለፍቅር እጅለእጅ መያያዝ አለብን”ብላለች።
የድምጻዊት ቻቺ ታደሰ “ደርሷል ሰዓቱ ” ነጠላ ዜማ ዛሬ ይፋ የተደረገ ሲሆን ግጥምና ዜማውን ራሷ ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ እና ወንድሟ ጳውሎስ ታደሰ የሰሩ ሲሆን ሚክሲንግና ማስተሪንጉን ኬኒ አለን ሰርቶላታል።
በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ለሀገራችን ለአህጉራችን ብሎም ለዓለማችን ፤ ዓለማቀፍ የሰላም ጥሪ ተላልፏል”።
አምስት የሙዚቃ አልበም ያላት ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ ይህ “ደርሷል ሰዓቱ” የተሰኘው ሙዚቃዋ ሶስተኛው ነጠላ ስራዋ ነው።
ለተጨማሪ: https://t.me/EventAddis1