ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በ”ኮራ አዋርድ”በአንደኝነት ምርጥ አምስት ውስጥ ገብቷል
ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በ”ኮራ አዋርድ”በ47.84 በመቶ በማምጣት ምርጥ አምስትን በአንደኝነት መቀላቀሉን የሽልማት ድርጅቱ ይፋ ካደረገው የደረጃ ሰንጠረዥ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
በ”እናትዋ ጎንደር” እና “ካሲናው ጎጃም” ባህላዊ ጣዕመ ሙዚቃዎችና በቅርቡ በተለቀቀው “አስቻለ” አልበም ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በኮራ አዋርድ “በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ዘርፍ” እጩ መሆኑ ይታወሳል።
ምርጥ የቡድን ሙዚቀኞች፣ ባህላዊ ሙዚቃ፣ ምርጥ ዲጄ፣ በምርጥ አርቲስት፣ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ ምርጥ የሴት እና የወንድ ዘፋኝን ጨምሮ 20 በሚሆኑ ዘርፎች ሽልማቱን አዘጋጅቷል።
አሸናፊው የሚወሰነው እኛ በምንሰጠው ድምጽ ስለሆነ ለድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ድምፃችሁን ለመስጠት የሚከተሉትን ሊንኮች ተጠቀሙ ተብላችኋል:-
1) በመጀመሪያ ሊንክ ይክፈቱት:-
https://www.koraawards.com/top40
2) ቀጥሎም በሚከፈተው ገፅ ወደ ግርጌ በመውረድ በምስል 1 ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመንካት የድምፅ መስጫውን ያግኙ፣
3) በመቀጠል ከሚመጣው የእጩዎች ዝርዝር ውስጥ በምስል 2 የተመለከተውን ይክፈቱት፣
4) በመጨረሻም በምስል 3 ላይ የተመለከተው የኢትዮጵያ እጩውን ምስል ያለበትን ያገኛሉ ፤ እሱን በመክፈት ድምፅ መስጠትዎን ያረጋግጡ ።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1