የአንጋፋው ደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ አዲስ መጽሐፍ በአማዞን ላይ ቀዳሚ ሆነ
የአንጋፋው ደራሲ ፍቅር ማርቆስ ደስታ”የሚሳም ተራራ” የተሰኘ የግለ ታሪክ አዲስ መጽሐፍ በአማዞን የሽያጭ ሰንጠረዥ በአፍሪካ ሥነጽሑፍ ከወጡት አዳዲስ መጻሕፍት ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ እየመራ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ደራሲው በማህበራዊ ትስስር ገፁ” ውድ አንባቢዎቼ! ደስ ብሎኛል እንኳን ደስ አላችሁ! አዲሱ መጽሐፍ ዛሬ በአማዞን ሽያጭ ሰንጠረዥ በአፍሪካ ሥነጽሑፍ ከወጡት አዳዲስ መጻሕፍት ቀዳሚውን ቦታ ይዟል! ካለ እናንተ አንባቢዎቼ እዚህ መድረስ አይቻልም ነበር! ከልቤ አመሰግናለሁ” ብሏል።
“የሚሳም ተራራ” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ የደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ የግለታሪክ መጽሐፉ ሲሆን ደራሲው የሕይወት ጉዞውን ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ፣ ከልጅነት እስከ ጐልማሳነት የተረከበት ነው ተብሏል።
ፍቅርማርቆስ ደስታ ከዚህ ቀደም “ከቡስካ በስተጀርባ”ን ጨምሮ በርካታ መጻሕፍት ለአንባቢያን አድርሷል።
አንጋፋው ደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ በሀገራችን ከተለመደው የድርሰት አፃፃፍ በተለየ መንገድ ለኢትዮጵያ ስነፅሁፍም ሆነ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም እድገት አይን ገላጭ ስራ ያበረከተ ጽሐፊ ነው።
መጽሐፉ ከመጋቢት 15 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዋልያ መጻሕፍት መከፋፈል ይጀምራል ።
Website: https://eventaddis.com/
Telegram: https://t.me/EventAddis1