የአፍሮ ኤዥያ ዓለምአቀፍ የጤና ኤክስፖ ሊካሄድ ነው
አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ “ድልድዮችን እንገንባ ህይወትን እናድን” በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ቀናት ከግንቦት 9 እስከ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም በኢግዚብሽን ማዕከል ይካሄዳል ተብሏል።
በአፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ ከሀገራችን እና ከተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የተወጣጡ ከ400 በላይ የጤና ተቋማትን፣የኢንዱስትሪ ባለሞያዎችን እና ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ እውቀት ለመለዋወጥ፣ ትብብርን ለማጎልበት እና የላቀ የጤና አጠባበቅ መፍትሄዎች ለማሳየት በርካታ ነፃ ምርምራዎችን በማህበረሰባችን ለመስጠት ያለው እንደሆነ ተገልጿል።
በአውደርዕዩ ላይ ዓለምአቀፍ የፓናል ውይይቶች፣ ወርክሾፖች፣ ኤግዚቢሽኖች፤ መዝናኛዎች፣ነፃ ስልጠናዎች ፣የግል እና የጋር ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በርካታ ሁነቶች ይካሄዳሉ ተብሏል።
በዚህ ዓለምአቀፍ ዝግጅት ላይ ከሰላሳ ሺ በላይ ለሚሆኑ ጎብኚዎች ነፃ የጤና ምርመራ እና የምክር አገልግሎቶች ይኖራሉ።ከ2000 በላይ የጤና ባለሞያዎች ይሳተፉበታል።
በተጨማሪም የጤና አጠባበቅ መሪዎችን ስኬቶችን እና አስተዋጽኦዎች ለማክበር የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት “ልዩ የጥቁር-ከረባት” የተሰኘ የእራት ግብዣ ሥነሥርዓት ይካሄዳል።
ይህ አውደርዕይ በኤፍ ዚ ማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ከሰላም ሔልዝ ኮንሰልታንሲ ጋር በመተባባር የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉን ያካተተ የእውቀት ልውውጥ ፣ ፈጠራ እና ትብብር መድረክ መፍጠር ሲሆን ይህም ባለድርሻ አካላትን ከተለያዩ አህጉራት በማሰባሰብ የዓለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ በጋራ የማሳደግ ዓላማ ይዟል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1