Author: Author

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ! መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቅሱ! 📍ሙዚቃ የድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም የድምጻዊው ዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። “ጋፊኮ” አልበም ስምንት የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። ጉቱ አበራ ከዚህ ቀደም ሀዋንሀዋ፣ ዴሚ፣ አነቱ፣ኢዮሌ የተሰኙ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሱ አይዘነጋም። የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) “ይንጋልሽ” የተሰኘ አዲስ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።14 ሙዚቃዎችን የያዘው አልበሙ ግጥም እና ዜማው በራሱ በወንዲ ማክ ተሰርቷል። በፍቅር፣ በማህበራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ተነግሯል።ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ…

Read More

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ! ሚዲያዎች መረጃውን ስትጠቀሙ ምንጭ ጥቀሱ❗️ 📍መጽሐፍ የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም አንድ መጽሐፍ በአንድ ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ለህትመት ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። “ቡና እና ምልኪ” የተሰኘውና ከዓመት በፊት ለንባብ ይበቃል ተብሎ የዘገየው መጽሐፍ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገፅ በሚደረግ ቅድም ክፍያ እንደሚታተም ገጣሚው አስታውቋል። ገጣሚው በማህበራዊ ትስስር ገፁ”በሀርድ ኮፒ ያጌጠ ምልኪና ቡና ከቅዳሜ ጀምሮ 1000 ኮፒ ህትመት በ1000 ብር ብቻ እጃችሁና የመጻሕፍት ሼልፋችሁ ላይ ለማኖር ዝግጅት አድርጉ” ብሏል። የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ “የጊዜ ሠሌዳ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን የቀረበ ሲሆን…

Read More

የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር “ዮቶር ድግስ” የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል። በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።…

Read More

“ምን ሆኛለሁ?” መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል የሥነልቦና ባለሞያዋ ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተጣመሩበት ‘ምን ሆኛለሁ?’ መፅሀፍ በጣም በቅርቡ ታትሞ ይወጣል ተብሏል። “የምታደርጉት ድርጊት ግራ አጋብቷችሁ ‘ምን ሆኛለሁ?’ ብላችሁ ከጠየቃችሁ ይሄ መፅሀፍ ልጅነታችሁን በመመርመር ራሳችሁን በተሻለ እንድትረዱ ያግዛችኋል”። በተጨማሪም “በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወይም በቲቪ የምታውቋቸው ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት አልገባ ብሏችሁ ‘ምን ሆኖ ነው?’ ወይም ‘ምን ሆና ነው?’ የሚል ጥያቄ ከፈጠረባችሁ ይሄ መፅሀፍ ጥሩ የፅንሰ ሀሳብ መነፅር ይሰጣችኋል ” ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። “ምን ሆኛለሁ” የተሰኘውን መጽሐፍ ብዙዎች መፅሀፉን ቀድመው እየገዙ እንደሆነም ተመልክተናል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Read More

“እያዩ ፈንገስ” ለሁለት ቀናት ብቻ ሊታይ ነው በበረከት በላይነህ ተደርሶ በግሩም ዘነበ የሚተውነው “እያዩ ፈንገስ” የአንድ ሰው  ተውኔት መድረክ ላይ መቅረብ ከጀመረ ዘንድሮ አስር ዓመት እንደሚሞላው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ይህንን የአስርኛ ዓመት ክብረበዓል በማሰብ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በራስ ሆቴል ለሁለት ቀናት ብቻ “እያዩ ፈንገስ” የአንድ ሰው ተውኔት ለታዳሚያን እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል። “እያዩ ፈንገስ” የአንድ ሰው ተውኔት “አጀንዳዬ” “ፌስታሌ” እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው “ቧልቲካ” በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Read More

የያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር በሆኑት ፕ/ር አሸናፊ ከበደ ስም የተሰየመው የጥበብ ማዕከል ተመረቀ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በመጀመርያ ዳሬክተርነት ባገለገሉበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በስማቸው የተሰየመው ፕሮፌሰር “አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል” ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ይህም የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል በርካታ ሙዚቀኞችን እና የሙዚቃ ታዳሚያንን መያዝ የሚችል ሲሆን በሀገራችን ለሙዚቃ ማቅረቢያ የተሰራ ግዙፍና የመጀመሪያው ማዕከል እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የሙዚቃ ሊቁ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ እና ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ሥራዎችን ያበረከቱ የሙዚቃ ሊቅ እንደነበሩ ይነገራል። እረኛው ባለዋሽንት፣ የኢትዮጵያ ሰላም፣ የፍቅር አንሰር ፣ የእሳት እራት፣…

Read More

አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ የሆነችበት “መቅረዝ ሥነኪን” የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም እረኛዬን ጨምሮ በተለያዩ ፊልሞቿና ድራማዎቿ የምናውቃት አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ የክብር እንግዳ ሆና የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Read More

የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል በልዩ ልዩ ሥነሥርዓት ይካሄዳል። በመዝጊያ ዝግጅቱም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራዝ ይሸለማሉ።ከተስፋ ጋር አብረው የሰሩ ድርጅቶችም እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል። ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በጎ ስራዎችን የጀመረው ከታህሳስ 1-29 ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር “በሊፍት ከፍዬ እሳፈራለሁ የጎዳና ልጅ አነሳለሁ” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ ነበር። ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር “ቤርሙዳ” የተሰኘውን ቴአትር፤ ሚያዚያ 28 ቀን “ሀሁ ወይም ፐፑ” ቴአትርን በልዩ ፕሮግራም ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪው…

Read More

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ “እነሆ ማሟሻ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ “እነሆ ማሟሻ” የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ያበቃል። ጋዜጠኛ መኮንን ወልደአረጋይ ስለመጽሐፉ በመግቢያው “በተለይም በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀረበ መሰናዶዎቹን ያደመጡና የተመለከቱ ወዳጆቼ ይህ ቁም ነገር ተሰንዶ በህትመት ቢቀርብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሳያስገነዘበ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እናም ዛሬ ጊዜው ደርሶ የመጀመሪያውን ቅጽና ለሌሎች ሥራዎች ዓይን ገላጭ የሆነውን “እነሆ ሟሟሻ” እንካችሁ ብያለሁ” ብሏል። መጽሐፉ በ200 ገፆች…

Read More

ወጣቷ ድምጻዊት ሀና ግርማ ”ባንተ ላይ” በተሰኘ ስራዋ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ድምፃዊት ሀና ግርማ ከ9 ወራት በፊት በሰራችው ስራ ከሰሞኑ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ። የተለያዩ ቪዲዮ ክሊፖችን እና ፊልሞችን ዳይሬክት እያደረገች የምትገኘው አዩ ግርማ ቪድዮውን ሰርተዋለች። አቡዱ ግጥምና ዜማውን ሰርቶ ታምሩ አማረ ሙዚቃውን አቀናብሮታል ። ሃና ግርማ ደግሞ በነሀሴ ወር 2015 ላይ አቀንቅናው በአንድ ግዜ በሙዚቃ አፍቃሪው ተወዳጅነትን አግኝቶላታል ። ”ባንተ ላይ”ሙዚቃው በናሆም ሪከርድስ በተለቀቀ 9 ወሩ 20 ሚሊዮን እይታ አግኝቷል።ይህም ኩባንያው ቪድዮዎችን መልቀቅ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል። ናሆም ሪከርድስ በዩቲዩብ ከለቀቃቸው ስራዎች በቀዳሚነት ላይ የሚገኘው የታሪኩ ጋንኪሳ ዲሽታ ጊና ሲሆን…

Read More