እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ ጥገና ሊደረግለት ነው።
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ የጥገና ስራ ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት መካከል የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በ15/08/2016 ዓ.ም የስራ ርክክብ ተደርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በጠበቀ መልኩ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፡፡የጥገና ስራው በተያዘለት የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ መጠገንና ለሃገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ስራ ተቋራጩ ይህን ታሪካዊ ቅርስ ጥገና ማድረግ በመቻላቸው እድለኛ እንደሆኑ ገልጸው ስራውን በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አከናውነው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡
እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ የጥገና ስራው ሲጠናቀቅ ምን እንደሚመስል 3D ቪዲዮ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች በማሳየት የውል ሥነ – ስርአቱና ርክክብ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1