“እብደት በህብረት” የተሰኘው የአንድ ተውኔት በቋሚነት ዘወትር ሀሙስ በ12:00 እና እሁድ በ8:00 በዓለም ሲኒማ መታየት ጀምሯል።
“ዕብደት በሕብረት” የአንድ ሰው ተውኔት በቶፊቅ ኑሪ ተደርሶ በዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ የተዘጋጀ የአንድ ሰው ተውኔት።
ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ የሚተውንበት”እብደት በህብረት” ተውኔት መቼቱን በሶስት መንግስታት ሥርዓት ላይ አድርጎ ከገፀ-ባህሪው ማንነትና ትዝታ ጋር ተመልካችን በማቆራኘት ይጠይቃል ይጎሽማል ያስቃል ያዝናናል።
በተጨማሪም በድምፅ (ሙዚቃ ግብዓት) በኩልም ከዘመኑ ጋር ተጣጥሞ እንዲታይ ጆርጋ መስፍን ተጠቦበታል።
“እብደት በህብረት” ቴአትር የተለያዩ መጠይቆችን በመጠየቅ ተመልካች የራሱን ሀሳብና የህይወት ምልከታ እንዲያስቀምጥ እድል የሚሰጥ ነው።
“እብደት በህብረት” የአንድ ሰዉ ቴአትር ሲሆን ባልተለመደ መልኩ “ተረፈ” የተሰኘ ድመት አብሮ ተውኖበታል።
Website: https://eventaddis.com/
Telegram: https://t.me/EventAddis1