Author: Author

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ጉባኤ በፈንድቃ ባህል ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስ፣ የባህል ድርጅት ( ዩኒስኮ ) ጋር በጋራ ያዘጋጁት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ተወዛዋዦች ጥበብ ማህበር ጉባኤ በፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል። ከባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ጉባኤ ዩኔስኮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከውጭ በመጡ የዘርፉ ባለሞያ “ዳንስ፣ ባህል እና ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የማኅበሩ አባላት እና ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበብ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ድግሪና የፒኤች ዲ ተመራቂዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ተብሏል፡፡ ሌሎች ክውን ጥበባት ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ…

Read More

የቅርስ ጉባኤና አውደርዕይ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የተዘጋጀው ዓመታዊ የቅርስ ምርምር ጉባኤና አውደርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ እና ረቡዕ ይካሄዳል። መርሐ ግብሩ ባለስልጣኑ ወደ ምርምር ተቋም መሸጋገሩን ተከትሎ የኢትዮጵያን ቅርስ ምርምር እና እንክብካቤ የ8ዐ ዓመታት ጉዞ መሰረት በማድረግ ከግንቦት 6 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በባለስልጣኑ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል። የተለያዩ የጥናትና የውይይት መነሻ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን የምርምር ዘርፉን ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ምክክር ይደረጋል መባሉ ተነግሯል። በተጨማሪም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከትናንት እስከዛሬ በየመስኩ ያለበትን ሁኔታ የሚያስቃኙ እና የሚዳስሱ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ ተገልጿል። የዚህ ዝግጅት የመክፈቻ ሥነሥርዓት ነገ ማክሰኞ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው የባለስልጣኑ ዋ/ና መስሪያ…

Read More

የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል አልበም አርብ ይለቀቃል የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል “ማያዬ” የተሰኘ  የመጀመሪያ አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል። በአልበሙ ላይ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በዜማ ኤልያስ መልካ ፣ አንተነህ ወራሽ ፣ ብስራት ሱራፌል፣ እሱባለው ይታየው(የሺ) ዘርዓ ብሩክ ሰማው የተሳተፉ ሲሆን በግጥሙ በኩል ወንድሰን ይሁብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው ሀብታሙ ቦጋለ፣ጥላሁን ሰማው እና ሌሎችም ተሳትፈዋል። በቅንብር አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ኤልያስ መልካ ፣ ሚካኤል ኃይሉ ፣ ታምሩ አማረ፣ ብሩክ ተቀባ፣ አዲስ ፍቃዱ በሌላ በኩል ሚክሲንግ እና ማስተሪንጉን ደግሞ ሰለሞን ኃ/ማርያም እንደሰሩ ተገልጿል። ድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል “የኛ” እና “እንደ እኛ”…

Read More

አርበኛ ወይዘሪት ሆይ ከበደች ስዩምን ለማስታወስ ልዩ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ሊካሄድ ነው በታሪካችን ሂደት ሴቶች ያላቸውን አስተዋፅኦ የሚዘክር ልዩ የፓናል ውይይት ከኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ጋር ታጅቦ ሊቀርብ ነው፡፡ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 3 2016 በወመዘክር አዳራሽ በሚደረገው መሰናዶ ላይ ልዩ ልዩ እንግዶች እንደሚታደሙ ይጠበቃል ተብሏል፡፡ የዚህ መሰናዶ ማስታወሻ የተደረገው ለአርበኛ ወይዘሪት ሆይ ከበደች ስዩም ሲሆን በዕለቱ አንጸባራቂ ገድላቸውን የሚያሳይ አጭር ድራማም ይቀርባል፡፡ በዕለቱ ከታሪክ፣ከህግ እና ከሥነ-ልቦና ሙያ የተወከሉ ባለሙያዎች ሴቶች በታሪክ ሂደት ውስጥ ያላቸውን አስተዋጽኦ በተመለከተ መነሻ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡ በዕለቱ ዶክተር ዘካሪያስ አምደብርሀን፣ሴቶችን ከኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር ይመለከታሉ፡፡ወይዘሮ ዮዲት አምሀ አበራ ደግሞ የሴቶችን የስነልቦና ጥንካሬ እና እንዴት ይበረታታሉ? የሚለው ላይ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ የህግ ባለሙያ ወይዘሮ ማሪያ ሙኒር…

Read More

እነሆ የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ 1.ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩና ድምጻዊት ሔለን በርሔ የተጣመሩበት “ዘመን” ኮንሰርት ቅዳሜ ግንቦት 3 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል።  2.ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ በቅርቡ የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንደሚያካሂድ አስታወቀ።ከወራት ፊት “ልዑል” የተሰኘ የሙዚቃ አልበሙን ያደረሰው ወጣቱ ድምጻዊ በቅርቡ ስለሚደረገው የሙዚቃ ኮንሰርቱ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፏል”በአልበም የወደዳችኋቸውን ሙዚቃዎቼን በቀጥታ ለእናንተ ለአድናቂ ወዳጆቼ ላቀርብላችሁ ዝግጅቴን እየጨረስኩ መሆኑን በደስታ እየገለፅኩኝ ስለ ሙዚቃ ድግሱ የበለጠ መረጃ በቅርብ ቀን ይጠብቁ” ብሏል። 3.የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል የመጀመሪያ አልበም የፊታችን ግንቦት 9 2016 ዓ.ም ይለቀቃል። በአልበሙ ላይ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን ግንቦት 9 በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል። ዘጠኝ ዓመትም እንደፈጀ ተነግሯል። 4.ድምጻዊ መሳይ…

Read More

የ2016 የሙዚቃ አልበሞችን ለማስታወስ ያህል በ2016 ዓ.ም ከመስከረም እስከ ሚያዝያ ባሉት ስምንት ወራት ብቻ “የሙዚቃ አልበም ጎርፍ” እስከ ሚባል ድረስ በርካታ የሙዚቃ አልበሞች ለአድማጮች ቀረበዋል። በቀሪዎቹ አራት ወራት ውስጥም ከአስር ያላነሱ ዝነኛ የሙዚቃ ባለሞያዎች የሙዚቃ አልበማቸውን ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከታማኝ ምንጭ ሰምቷል። በ2016 ዓ.ም ከተለቀቁ በርካታ የሙዚቃ አልበሞች ውስጥ የአስራ አምስቱን ብቻ የሚያዝያ ወር ከመጠናቀቁ አስቀድሞን እናስታውሳችዋለን። 1.ልዑል ሲሳይ “ልዑል” አልበ 2.የማርያም ቸርነት (የማ) “የደጋ ሰው” አልበም 3.አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) “አስቻለ” አልበም 4.ማስተዋል እያዩ “እንዚራ” አልበም 5.ስንሻው ለገሰ “እንደራሴ” አልበም 6.ዳዊት ቸርነት “ሕይወት ሰው ክፍል 2” አልበም 7.ሮፍናን ኑሪ “ዘጠኝ: ሔራንቤ እና ኖር” አልበሞች 8.ጀንበሩ ደመቀ…

Read More

በእይታ ላይ የሚገኙ ቴአትሮች ዝርዝር በአዲስ አበባ ከተማ በቋሚነት ሁለት የቴአትር ማሳያዎች ብቻ በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ። እነዚህም የቴአትር ማሳያዎች አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና ዓለም ሲኒማ ናቸው። በአጠቃላይ እንደሀገር ዘጠኝ ተውኔቶች ብቻ በቋሚነት እየቀረቡ እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በእይታ ላይ የሚገኙ ተውኔቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል። ☑️ ሶስቱ አይጦች ድርሰት: ኤልያስ ተስፋዬአዘጋጅ: ካሌብ ዋለልኝቀን: ማክሰኞሰዓት: 11:30ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር ☑️ ሀሁ ወይንም ፐፑ ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንአዘጋጅ: ተስፋዬ ሲማቀን: ረቡዕሰዓት: 11:30ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር ☑️ ሸምጋይ ድርሰት:ታደለ አያሌውአዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬቀን: ሐሙስሰዓት: 11:30ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር ☑️ የሁለት ጌቶች አሽከር አዘጋጅ:ጂያንሉካ ባርባዶሪቀን: አርብሰዓት: 11:30ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር ☑️ ባሎች እና ሚስቶች ድርሰት: ውዱ…

Read More

እነሆ የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ 1.”ግራ ቀኝ” አስቂኝ ድራማ በምዕራፍ ሁለት ሊመለስ ነው። አርቲስት አበበ ባልቻ ፣ አርቲስት ሚካኤል ታምሬ እና አርቲስት ግሩም ዘነበ የተጣመሩበትና ተጋባዥ ተዋናኒያን የሚሳተፉበት”ግራ ቀኝ” የተሰኘ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 27 2016 ዓ.ም በፋሲካ ዕለት በምዕራፍ ሁለት ይመለሳል። ድራማውም በኢቲቪ ዜና እና መዝናኛ ቻናል ለዕይታ ይበቃል ተብሏል። 2.”የፍቅር ካቴና” የተሰኘ ተውኔት ከአስር ዓመት በኃላ በድጋሚ የፊታችን ግንቦት 2 2016 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ወደ መድረክ ይመለሳል።በአርቲስት ወይንሸት አበጀ ፕሮዲዩስ የተደረገው ይህ “የፍቅር ካቴና” ተውኔት ድርሰትና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንንት ፅጌ ነው።በተውኔቱ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ሚኪ ተስፋዬ ፣ ወይንሸት አበጀ ፣አሸናፊ ማህሌት በተዋናይነት ይሳተፉበታል። 3.ድምጻዊ ጃኪ ጎሲ ከበርካታ…

Read More

የአንጋፋዋ ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ “ደርሷል ሰዓቱ” የተሰኘ አዲስ ሙዚቃ ከአስር ዓመት በኃላ ዛሬ ሚያዝያ 18 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በቻቺ ታደስ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ተለቋል። የአንጋፋዋ የበጎፈቃድና የሰላም አምባሳደር ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ “ሰማያችን ሊጠራ ጉም ተኖ ከአድማስ ማዶ እየተፍለቀለቀች እንደምትወጣ የፈካች ውብ ጸሀይ ልትወጣ ይሄው “ደርሷል ሰዓቱ ” ምርታችን ሊያብብ አዝመራችን ሊያጠግበን ሰላማችን ሊበዛ ይሄው “ደርሷል ሰዓቱ” እንድንል የሚያስችለን ብሩህ ዘመን ለሁላችንም እንዲመጣልን ሁላችንም ለሰላምና ለፍቅር እጅለእጅ መያያዝ አለብን”ብላለች። የድምጻዊት ቻቺ ታደሰ “ደርሷል ሰዓቱ ” ነጠላ ዜማ ዛሬ ይፋ የተደረገ ሲሆን ግጥምና ዜማውን ራሷ ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ እና ወንድሟ ጳውሎስ ታደሰ የሰሩ ሲሆን ሚክሲንግና ማስተሪንጉን ኬኒ አለን ሰርቶላታል። በጋዜጣዊ…

Read More

“ቱሉ ፎርሳ” ቱሉ ሠላሳ ዓመቱ ነው።ወይም ወደዚያ ግድም ነው። እና ቱሉ ቁመቱ ረጅም ነው። የቱሉ እጆች ትላልቅ ናቸው።የቱሉ ክንዶች ጠንካሮች ናቸው።የቱሉ መዳፎች ሸካራ ናቸው። ቱሉ ከማካሮኒ ፣ፓስታና ፓስቲኒ ፋብሪካ ውስጥ ወፍጮ ክፍል ነው የሚሠራው። ወፍጮ ክፍል ስድስት ዓመት ሠርቷል።..የፋብሪካው ባለቤት ሙሴ ጋሌብ ናቸው። ጌታ ጋሌብ እዚች ሃገር (ይቺው የኛይቱ የምንላት)ሲገቡ ቤሳቤስቲን አልያዙም።እዚህ ከገቡ በኋላ ነው ይህንን ሁሉ ያፈሩት፣ ያንን ሁሉ ቪላ ሠርተው የሚያከራዩት፣ያንን ሁሉ ሱቅ የከፈቱት። ጌታ ጋሌብ የናጠጡ ዲታ ናችው።አቤት ሠራተኛ ሲፈራቸው።ጌታ ጋሌብ ሽማግሌ ናቸው።አጭር ፣መላጣ ባርኔጣ የማይለያቸው አማርኛ አቀላጥፈው የሚያውቁ ዕድላም ሰው ናቸው። ሰለ አበሻ ሲናገሩ <<አበሻ ሥራ አይወድም።አበሻ ሠነፍ ነው።ለዚህ ነው ሃብታም የማይሆነው እንደኔ>>ይላሉ።….ቱሉ ፎርሳ በወር ሠላሳ…

Read More