Author: Author

ጥቂት ከጥበብ ማዕድ: በገብረክርስቶስ ደስታ በኩል በአሳፋ ሀይሉ በህይወት አጋጣሚ የተነሣ ወደ ሥራዎቹና ህይወቱ በጥናት ዘልቄ በመግባት የተነሣ፣ እጅግ ጥልቅ አድናቆት፣ ፍቅርና ርህራሄን በልቤ እንዳሳድርለት ያደረገኝ አንድ ሠዓሊና ገጣሚ አለ። ገብረክርስቶስ ደስታ ነገዎ። ደግሞ ይግረምህ ሲለኝ እርሱም የሐረር ልጅ ነው። ስለ ገብረክርስቶሥ ህይወትና ሥራዎች ይበልጥ በስፋት በሕዝብ ዘንድ እንዲታወቅ ትልቅ ሚና ከተጫወቱት አካሎች መሐል በቀዳሚነት የምጠራው፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የጀርመንን የባህል ማዕከል (Goethe Institute) ነው። ሠዓሊው የተናዘዛቸውን 30 ሥዕሎች ከጀርመን ሀገር ከሚዩኒክ የህዝብ ሙዝየም ድረስ አምጥቶ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአደራ ያስረከበ ተቋም በመሆኑ ለገተ ኢንስቲትዩት ታላቅ አክብሮት አለኝ። የገብሬን ሥራዎች ከተሰደዱበት ሲመልስ ደግሞ እንዲሁ ባንዴ አልነበረም። ነፍሱን ይማረውና የገብሬ ተማሪ…

Read More

በእያዩ ፈንገስ ቲያትሮች ማህበራዊ ሂስን በጨዋታና ስላቅ ሲያቀርብ እናውቀዋለን። ኅርየት ፊልምን ሲሰራ አማኑኤል ሆስፒታል ለወራት ተመላልሷል። ስለ አእምሮ ህክምና የግንዛቤ መስጫ ዝግጅቶች ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ይሳተፋል። ተዋናይ ግሩም ዘነበ። የአእምሮ ጤና የሬዲዮ ዝግጅታችን ላይ ስለፊልም፣ ቲያትር እና አእምሮ ጤና በጨዋታ እያዋዛ ጥሩ መልእክቶች አስተላልፏል። ~”…አንዳንድ ጊዜ ሳስበው በነፃነት የመናገር ባህላችን ስላልዳበረ ደራሲዎች መናገር የሚፈልጉትን የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው ላይ የሚሸጉጡት ይመስለኛል። እኔ ተወልጄ ያደግኩት ሀረር ነው። ሰዎች በነፃነት ግልፁን ይናገራሉ። ከወደዱህ ወደዱህ ነው ከጠሉህም ፊትለፊት ነው። ሀረር ሄደህ ፊልም ብትሰራ የአእምሮ ህመም ያለበት ገፀ ባህሪ አያስፈልግህም። በግልፅ የመናገር ባህል ብናዳብር ፀሀፊዎች የአእምሮ ህሙማን ላይ መሸጎጣቸው እየቀረ የሚመጣ ይመስለኛል…” ~”ሀገራችን ውስጥ…

Read More

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን አዲስ አልበም በግንቦት ወር ለአድማጮች ይደርሳል። የታዋቂው ሙዚቀኛ ፣ አሬንጀርና ፕሮዲውሰር ጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘ አዲስ አልበም ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በዲጂታል መተግበሪያዎች ይለቀቃል ተብሏል።‘ ከሁሉ የላቀው ደግ’ በተለይም የኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ይዘቶች ጋር መንፈሳዊነትን በማዋሃድ ኢትዮ ጃዝን የሚያስቃኝ አልበም ነው ተብሏል። “የነጋሪት ባንድ” ባንድ አልበም የፊታችን እሁድ ይመረቃል።የተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ሙዚቃን በአንድ የያዘው “ነጋሪት ባንድ” የሀገርበቀል የጃዝ የሙዚቃ አልበም የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 19 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ውስጥ ይመረቃል።በዕለቱም ተፈሪ አሰፋ ፣ ጆርጋ መስፍን ፣ አብይ ተክለማርያምን ጨምሮ…

Read More

ድምጻዊት መክሊት ሀደሮ “ኢትዮ ብሉ” የተሰኘ ግሚስ የሙዚቃ አልበም ከሰሞኑ ለአድማጮች አድርሳለች መክሊት ሀደሮ እንግሊዘኛ ቀመስ በሆነ አማርኛ፣ አፍሮዋን አበጥራ፣ መድረክ ላይ በወንበር ቁጭ ብላ ዳንስና ወግ በቀላቀለ አኳኋን ‹‹ከመከም ጎፈሬ›› የሚለውን ሀገርኛ ዜማ ስትጫዎት በብዙኃኑ አእምሮ ውስጥ ሰርጻለች፡፡ ስድስት ዜማዎችን የያዘ በዘመኑ ‹‹ግማሽ አልበም›› ተብሎ የሚታወቀውን ዓይነት አልበም ሰሞኑን ለአድናቂዎቿ ማድረስ የቻለችው መክሊት ይሄንን ሥራ ጀምሮ ለመጨረስ አምስት ዓመታት እንዳስፈለጓት ለኤፍ ኤም አዲስ የመሰንበቻ ፕሮግራም ዝግጅት ገልጻለች፡፡ ሥራው አምስት ዓመታት ሊፈጅ የቻለው አንድም የመጀመሪያ ልጇን ያገኘችው ከአራት ዓመታት በፊት በመሆኑ አንድም የኮቪድ ወረርሽኝ ብዙ ሥራዎችን ስላስተጓጎለ መሆኑን ገልጻለች፡፡ ‹‹ኢትዮ ብሉ›› በሚል ስያሜ ለአድማጭ የቀረበው አልበሙ የአሜሪካዎቹ ጃዝና ብሉዝ የሙዚቃ…

Read More

ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በ”ኮራ አዋርድ”በአንደኝነት ምርጥ አምስት ውስጥ ገብቷል ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በ”ኮራ አዋርድ”በ47.84 በመቶ በማምጣት ምርጥ አምስትን በአንደኝነት መቀላቀሉን የሽልማት ድርጅቱ ይፋ ካደረገው የደረጃ ሰንጠረዥ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል። በ”እናትዋ ጎንደር” እና “ካሲናው ጎጃም” ባህላዊ ጣዕመ ሙዚቃዎችና በቅርቡ በተለቀቀው “አስቻለ” አልበም ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በኮራ አዋርድ “በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ዘርፍ” እጩ መሆኑ ይታወሳል። ምርጥ የቡድን ሙዚቀኞች፣ ባህላዊ ሙዚቃ፣ ምርጥ ዲጄ፣ በምርጥ አርቲስት፣ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ ምርጥ የሴት እና የወንድ ዘፋኝን ጨምሮ 20 በሚሆኑ ዘርፎች ሽልማቱን አዘጋጅቷል። አሸናፊው የሚወሰነው እኛ በምንሰጠው ድምጽ ስለሆነ ለድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ድምፃችሁን ለመስጠት የሚከተሉትን ሊንኮች ተጠቀሙ ተብላችኋል:- 1) በመጀመሪያ ሊንክ ይክፈቱት:-https://www.koraawards.com/top40 2) ቀጥሎም…

Read More

የአፍሮ ኤዥያ ዓለምአቀፍ የጤና ኤክስፖ ሊካሄድ ነው አፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ “ድልድዮችን እንገንባ ህይወትን እናድን” በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ቀናት ከግንቦት 9 እስከ ግንቦት 11 2016 ዓ.ም በኢግዚብሽን ማዕከል ይካሄዳል ተብሏል። በአፍሮ ኤዥያ ዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ ከሀገራችን እና ከተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የተወጣጡ ከ400 በላይ የጤና ተቋማትን፣የኢንዱስትሪ ባለሞያዎችን እና ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ እውቀት ለመለዋወጥ፣ ትብብርን ለማጎልበት እና የላቀ የጤና አጠባበቅ መፍትሄዎች ለማሳየት በርካታ ነፃ ምርምራዎችን በማህበረሰባችን ለመስጠት ያለው እንደሆነ ተገልጿል። በአውደርዕዩ ላይ ዓለምአቀፍ የፓናል ውይይቶች፣ ወርክሾፖች፣ ኤግዚቢሽኖች፤ መዝናኛዎች፣ነፃ ስልጠናዎች ፣የግል እና የጋር ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በርካታ ሁነቶች ይካሄዳሉ ተብሏል። በዚህ ዓለምአቀፍ ዝግጅት ላይ ከሰላሳ ሺ በላይ ለሚሆኑ ጎብኚዎች…

Read More

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ ጥገና ሊደረግለት ነው። እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ የጥገና ስራ ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት መካከል የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በ15/08/2016 ዓ.ም የስራ ርክክብ ተደርጓል። በፕሮግራሙ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በጠበቀ መልኩ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፡፡የጥገና ስራው በተያዘለት የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ መጠገንና ለሃገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ስራ ተቋራጩ ይህን ታሪካዊ ቅርስ ጥገና ማድረግ…

Read More

የአርቲስት አማኑኤል ሐብታሙ እስርና አንዳንድ መረጃዎች አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በትላንትናው ዕለት በፖሊስ መታሰሩ ይታወሳል።ከአርቲስቱ እስር ጋር በተያያዘ የፊልም ባለሞያው ያሬድ ሹመቴ ተከታዩን መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ጽፎ ተመልክተናል። “ከቤተሰቦቹ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ይህንን ማስታወሻ እስካሰፈርኩበት ሰዓት ድረስ አማኑኤል ፖሊሶች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ወስደውት በእስር ላይ ይገኛል። ቤተሰቦቹ ራት እንዳደረሱለት እና በፖሊስ ስለተያዘበት ጉዳይ እርሱም ይሁን በሕግ ስር የዋሉት ፖሊሶች ምንም አይነት መረጃ እንዳልሰጧቸው አረጋግጫለሁ። አማኑኤል ሐብታሙ “እብደት በሕብረት” የተሰኘውን ተወዳጅ አዲስ ባለ አንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቴአትሩን እስራኤል አገር ለሚገኙ ተመልካቾች ለማሳየት በጉዞ ላይ ሳለ ትላንት ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም አመሻሽ ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በፖሊስ…

Read More

ገጣሚ ለምን ሲሳይ በዘ-ብሪትሽ ቡክ ሽልማት ታጨ ትውለደ ኢትዮጵያዊው የሥነጽሑፍ ባለሞያ ለምን ሲሳይ በዘ ብሪትሽ ቡክ አዋርድ ላይ” let the light  pour in “በተሰኘው መጽሐፉ እጮ ሆኗል። ገጣሚ ለምን ሲሳይ”በዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ ፣ የአኗኗር ዘይቤ እና ኢላስትሬድ” በተሰኘው ዘርፍ ውስጥ እንደታጨ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። ከኢትዮጵያዊ እናት የተገኘው ገጣሚ ለምን ሲሳይ በቅርቡ የብሪታኒያ መንግሥት በሙያቸው ብዙ ላበረከቱ ሰዎች የሚሰጠውን ክብር ከልዑል ቻርልስ እጅ ተቀብሏል። ለምን የመጀመሪያውን የግጥም መድብሉን የ21 ዓመት ወጣት ሳለ ነው ያሳተመው። ‘ማይ ኔም ኢዝ ዋይ’ አሊያም በግርድፍ ትርጉሙ ‘ስሜ ለምን ነው’ በተሰኘው መፅሐፉ የብሪታኒያን የሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከላትን ታሪክ ልቅም አድርጎ ይተነትናል። በፈረንጆቹ 1995 ኢንተርናል ፍላይት የተሰኘ ዘጋቢ…

Read More

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥለው ይቀርባሉ 1.”መቅረዝ ሥነኪን” የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 10 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ፍቃዱ አየልኝ ፣ ሔለን ቢዛ፣ ሰለሞን ሽፈራው ፣መሐመድ እድሪስ፣ ቴዎድሮስ ካሣ ፣ አቡ የአብ ፣ ኪሩቤል ጌታቸውና ሌሎችም የሥነጽሐፍ እና ኪነጥበብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።በተጨማሪም ትላልቅ ስራ የሰሩ የኪነጥበብ ሰዎች የሚዘክሩበት እና የክብር እንግዳ የሚገኘበት መሰናዶ ነው።በዚህ የኪነጥበብ መርሐግብር ላይ ለመታደም በሰዓቱ መገኘት በቂ ነው። 2.”ፍትሕ ምንድነው ?” የተሰኘ የሀሳብ ውይይት የፊታችን ሚያዝያ 12 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ 5 ኪሎ በሚገኘው አፄ ናኦድ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። የተለያዩ የፍትህ ዓይነቶች የፍትህ ምንጫቸው ምንድነው በሚል ርዕስ በፍሬው ማሩፍ…

Read More