የፐርፐዝ ብላክ ” Invest in Poverty Intiative” የተሰኘ አዲስ ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ
ፐርፐዝ ብላክ በዛሬዉ ዕለት ሰዎች በየወሩ 100 እና ከዚያህ በላይ ብር የሚቆጥቡበት”Invest in Poverty Intiative” የተሰኘ ዘመቻ አስጀምሯል።
ፐርፐዝ ብላክ በዚህ ዘመቻ ተጠቃሚዎች በየወሩ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ገንዘብን በመቆጠብ ከፍ ያለ ትርፍ የሚያገኙበት አሰራር እንደሆነ አስታውቋል።
ተቋሙ በዚሁ መርሐግብር ላይ እንዳሳወቀዉ በአሁኑ ወቅት ካፒታሉ 2.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ነው። የፐርፐዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ እሸቱ(ዶ/ር) ሰዎች የሚያስቀምጡት ገንዘብ በዝግ ሂሳብ የሚቀመጥና ባሻቸዉ ጊዜ ወጪ የሚያደርጉበት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ አዲስ አሰራር መሰረት ተቋሙ በቀጣዮቹ አምስት አመታት 100 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ማቀዱንም ይፋ አድርገዋል።
ቆጣቢዎች በተለመፈዉ የባንክ ቁጠባ ከሚያገኙት 7 በመቶ ወለድ በተሻለ በዚህ የቁጠባ ስርዓት 10 በመቶ ወለድ ተከፋይ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
ከሕብረት ባንክ 19 በመቶ ወለድን ለተቋሙ የሚያቀርብ ሲሆን በጋራ ይሰራል ባሉት ስራም ፐርፐዝ ብላክ 9 በመቶ ድርሻ እንደሚያገኝ ጠቅሰዋል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1