የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ “እነሆ ማሟሻ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል
ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ “እነሆ ማሟሻ” የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ያበቃል።
ጋዜጠኛ መኮንን ወልደአረጋይ ስለመጽሐፉ በመግቢያው “በተለይም በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀረበ መሰናዶዎቹን ያደመጡና የተመለከቱ ወዳጆቼ ይህ ቁም ነገር ተሰንዶ በህትመት ቢቀርብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሳያስገነዘበ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እናም ዛሬ ጊዜው ደርሶ የመጀመሪያውን ቅጽና ለሌሎች ሥራዎች ዓይን ገላጭ የሆነውን “እነሆ ሟሟሻ” እንካችሁ ብያለሁ” ብሏል።
መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1