የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል
የተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረበዓል የመዝጊያ ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል በልዩ ልዩ ሥነሥርዓት ይካሄዳል።
በመዝጊያ ዝግጅቱም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራዝ ይሸለማሉ።ከተስፋ ጋር አብረው የሰሩ ድርጅቶችም እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ 25ተኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በጎ ስራዎችን የጀመረው ከታህሳስ 1-29 ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር “በሊፍት ከፍዬ እሳፈራለሁ የጎዳና ልጅ አነሳለሁ” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ ነበር።
ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር “ቤርሙዳ” የተሰኘውን ቴአትር፤ ሚያዚያ 28 ቀን “ሀሁ ወይም ፐፑ” ቴአትርን በልዩ ፕሮግራም ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪው አቅርቧል፡፡
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1