ወጣቷ ድምጻዊት ሀና ግርማ ”ባንተ ላይ” በተሰኘ ስራዋ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች
ድምፃዊት ሀና ግርማ ከ9 ወራት በፊት በሰራችው ስራ ከሰሞኑ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ።
የተለያዩ ቪዲዮ ክሊፖችን እና ፊልሞችን ዳይሬክት እያደረገች የምትገኘው አዩ ግርማ ቪድዮውን ሰርተዋለች። አቡዱ ግጥምና ዜማውን ሰርቶ ታምሩ አማረ ሙዚቃውን አቀናብሮታል ። ሃና ግርማ ደግሞ በነሀሴ ወር 2015 ላይ አቀንቅናው በአንድ ግዜ በሙዚቃ አፍቃሪው ተወዳጅነትን አግኝቶላታል ።
”ባንተ ላይ”ሙዚቃው በናሆም ሪከርድስ በተለቀቀ 9 ወሩ 20 ሚሊዮን እይታ አግኝቷል።ይህም ኩባንያው ቪድዮዎችን መልቀቅ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል።
ናሆም ሪከርድስ በዩቲዩብ ከለቀቃቸው ስራዎች በቀዳሚነት ላይ የሚገኘው የታሪኩ ጋንኪሳ ዲሽታ ጊና ሲሆን 35 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ይህ ስራ በዚህ ቁጥር የታየው በ3 አመት ውስጥ ነው። የሃና ግን በ9 ወራት ነው 20,000,000 የታየው። የቬሮኒካ አዳነ “ጥፍጥ አለኝ” ከሁለት አመት በፊት ተለቆ 18 ሚሊየን ጊዜ ታይቶ ናሆም ከለቀቃቸው ስራዎች ብዙ እይታ በማግኘት 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
📍መረጃው የሁሉ አዲስ ነው።
ለተጨማሪው: @EventAddis1