“ምን ሆኛለሁ?” መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል
የሥነልቦና ባለሞያዋ ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተጣመሩበት ‘ምን ሆኛለሁ?’ መፅሀፍ በጣም በቅርቡ ታትሞ ይወጣል ተብሏል።
“የምታደርጉት ድርጊት ግራ አጋብቷችሁ ‘ምን ሆኛለሁ?’ ብላችሁ ከጠየቃችሁ ይሄ መፅሀፍ ልጅነታችሁን በመመርመር ራሳችሁን በተሻለ እንድትረዱ ያግዛችኋል”።
በተጨማሪም “በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወይም በቲቪ የምታውቋቸው ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት አልገባ ብሏችሁ ‘ምን ሆኖ ነው?’ ወይም ‘ምን ሆና ነው?’ የሚል ጥያቄ ከፈጠረባችሁ ይሄ መፅሀፍ ጥሩ የፅንሰ ሀሳብ መነፅር ይሰጣችኋል ” ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
“ምን ሆኛለሁ” የተሰኘውን መጽሐፍ ብዙዎች መፅሀፉን ቀድመው እየገዙ እንደሆነም ተመልክተናል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1