Author: Author

ጋዜጠኞችና ደራሲያን ዕውቅና ሊሰጣቸው ነው ቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን “ክብር” የተሰኘ የደራሲያንና የጋዜጠኞች ሽልማት ዕውን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በደራሲና ጋዜጠኛ ቃል ኪዳን ኃይሉ በ2015 ዓም ተመስርቶ “ክብር ሽልማት” ለማዘጋጀት አስር የቦርድ አባላትን አዋቅሮ የተጀመረ ድርጅት ነው። አበረ አዳሙ ( የደራስያን ማኅበር ፕሬዝዳንት)፣ አቶ አገኘሁ አዳነ ( በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአለ ሥነ ጥበብና ሥነ ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር) ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ( ሰአሊና ቀራጺ)፣ አቶ ጥበቡ በለጠ ( የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት)፣ ዶ/ ር ተሻገር ሽፈራው (፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህር)፣ ዮናስ ሐጎስ ( ጋዜጠኛ)፣ አዳነች ወ/ ገብርኤል ( አርቲስት)፣ ሰለሞን አለሙ…

Read More

የአንጋፋው ደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ አዲስ መጽሐፍ በአማዞን ላይ ቀዳሚ ሆነ የአንጋፋው ደራሲ ፍቅር ማርቆስ ደስታ”የሚሳም ተራራ” የተሰኘ የግለ ታሪክ አዲስ መጽሐፍ በአማዞን የሽያጭ ሰንጠረዥ በአፍሪካ ሥነጽሑፍ ከወጡት አዳዲስ መጻሕፍት ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ እየመራ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል። ደራሲው በማህበራዊ ትስስር ገፁ” ውድ አንባቢዎቼ! ደስ ብሎኛል እንኳን ደስ አላችሁ! አዲሱ መጽሐፍ ዛሬ በአማዞን ሽያጭ ሰንጠረዥ በአፍሪካ ሥነጽሑፍ ከወጡት አዳዲስ መጻሕፍት ቀዳሚውን ቦታ ይዟል! ካለ እናንተ አንባቢዎቼ እዚህ መድረስ አይቻልም ነበር! ከልቤ አመሰግናለሁ” ብሏል። “የሚሳም ተራራ” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ የደራሲ ፍቅርማርቆስ ደስታ የግለታሪክ መጽሐፉ ሲሆን ደራሲው የሕይወት ጉዞውን ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ፣ ከልጅነት እስከ ጐልማሳነት የተረከበት ነው ተብሏል። ፍቅርማርቆስ ደስታ ከዚህ ቀደም…

Read More

አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ እና አለልኝ መኳንንት ፅጌ ከበርካታ ዓመታት በኃላ ወደ ቴአትር ሊመለሱ ነው በበርካታ ተከታታይ ድራማዎች፣ ፊልሞችና ተውኔቶች የምናውቃቸው አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ እና አለልኝ መኳንንት ፅጌ ” የፍቅር ካቴና” በተሰኘ ተውኔት በድጋሚ ወደ ቴአትር ሊመለሱ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። በአርቲስት ወይንሸት አበጀ ፕሮዲዩስ የተደረገው ይህ “የፍቅር ካቴና” ተውኔት ድርሰትና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንንት ፅጌ ነው። በተውኔቱ ላይ ከአርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ በተጨማሪም ሚኪ ተስፋዬ ፣ ወይንሸት አበጀ ፣ አሸናፊ ማህሌት በተዋናይነት ይሳተፉበታል። በቅርቡም ተውኔቱ ለመድረክ ይበቃል። Website: https://eventaddis.com/ Telegram: https://t.me/EventAddis1

Read More

“ልዕልት” የሥዕል አውደርዕይ በእይታ ላይ ይገኛል የሠዓሊ መርዕድ ታፈሰ “ልዕልት” የሥዕል አውደርዕይ መጋቢት 6 2016 ዓ.ም ጎላ ፓርክ በሚገኘው  ቅዱስ ጊዮርጊስ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል። በዚህ አውድርዕይ የሠዓሊ መርዕድ ታፈሰ የ25 ዓመታት የሥዕል ስብስቦችን ያካተቱ ከ150 ስራዎች በላይ የሥዕል ስራዎች ቀርበዋል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ መጋቢት 27 2016 ዓ.ም ለእይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል። Website: https://eventaddis.com/ Telegram: https://t.me/EventAddis1 Telegram: https://t.me/Eve

Read More

ሁለተኛው የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሽፕ በይፋ ተከፍቷል። ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ የትምህርትና የስልጠና ማዕከል ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር  ያዘጋጀው ሁለተኛው የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሽፕ ከመጋቢት 5  እስከ 7 ቀን 2016 ዓ/ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። በውድድሩ ላይ የተለያዩ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተማሪዎች እየተሳተፉ ነው። በዚህ የሮቦቲክስ ውድድር አሸናፊ የሚሆኑት የዋንጫ ፣ የምስክር ወረቀት የሚሰጣቸው ሲሆን በተጨማሪም በአሜሪካ ዳላስ በሚካሄደው የዓለምአቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር የመወዳደር እድል ያገኛሉ ተብሏል። ኢሌሌ ሆቴል 7ተኛ ፎቅ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው በእዚህ ልዩ ኩነት ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣት እስከ መጋቢት 7 2016 ዓ.ም መታደም እንደሚችሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።…

Read More

ሰዋሰው  መልቲሚዲያ  እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአጋርነት ስምምነት አደረጉ ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ የሙዚቃ አልበሞችን በጋራ ለማሳተም የሚያስችል አጋርነት መመስረታቸውን ይፋ አደረጉ። ከሰዋሰዉ ድምፃዉያን መካከል አንዱ የሆነዉ እና ከፋሲካ በዓል በኋላ የሚለቀቀዉን የአማኑኤል ሙሴ አልበም ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የስፖንሰርሺፕ ድርሻዉን ውሰዷል። በዝናር ዜማ የድምፃዉያን ስብስብ እራሱን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀዉ አማኑኤል ሙሴ ድንቅ ችሎታና አቅም ያለዉ ተስፈኛ ወጣት ድምፃዊ መሆኑ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ‘’ጥቁር ዉሃ’’ የተሰኘዉ አልበሙም በሳፋሪኮም አጋርነት በሰዋሰዉ አፕ የሚለቅቅ መሆኑ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪ ወጣት ሴት ድምፃዊ አልበምን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስፖንስር እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን የድምፃዊቷን ማንነት ግን በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ድምፃዉያኑ በመልቲሚዲያው…

Read More

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥለው ይቀርባሉ 1.ከተለመዱት ዘውጎች ወጣ ያለ የፊልም ይዘት ይዞ የመጣው “6:00 ሰዓት ከሌሊቱ ” ፊልም ባሳለፍነው ሰኞ ተመርቋል።ይህ የትሪለር ዘውግ ያለው ፊልም ከሰባት በላይ ቦታዎችን መቼቱ አድርጓል። ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ዓመት ገደማ የፈጀ ሲሆን ፤ አርቲስት ሠላም ተስፋዬ ፣ አርቲስት ሚኪ ተስፋዬና ሌሎች የፊልም ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በሀይሉ እንግዳ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ሲሆን በሀይሉ እንግዳ እና በሸነና ቦሩ የፊልሙ ኤክኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰሮች ናቸው። መጋቢት 6,7,8 እንዲሁም መጋቢት 13, 14 , 15 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል። 2.የኮሜዲያን እሸቱ መለሰ “ማን እንደ ሀገር ” የተሰኘ የኮሜዲ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ውስጥ…

Read More

አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 አንድ ዓመት ሞላው አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በተሟላ አቅም መተሟላ አቅም መደበኛ ስርጭቱን በይፋ የጀመረበትን አንደኛ ዓመት ዛሬ መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም እያከበረ ይገኛል። በቀጣይ ጣቢያው አሁን ካሉት ይዘቶች በተጨማሪ ተደራሽነቱን ይበልጥ የሚያሰፉና ተቀባይነቱንም የሚያሳድጉ አዳዲስ ጉዳዮችን ለመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ከሬዲዮ በተጨማሪ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹም አዳዲስ ይዘቶቹን ደረጃ በደረጃ እንደሚያቀርብ ገልጿል። በመዝናኛ እና በቢዝነስ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በመዝናኛው ዘርፍ በአድማጮች ዘንድ በሬዲዮ ድራማ ያለውን ሰፊ ፍላጎት ለመመለስ ላለፉት 40 ዓመታት በሬዲዮ ድራማዎቹ በሰራቸው ስራዎች ከሚታወቀው አንጋፋውና ተወዳጁ ደራሲ፣ አዘጋጅና ተዋናይ ኃይሉ ፀጋዬ ጋር አዲስ የሬዲዮ ድራማ ለማቅረብ የሚያስችል…

Read More

የወመዘክር አውደርዕይ በእይታ ላይ ይገኛል የኢትዮጵያን ታሪክ በፎቶ የሚተርከው “በፎቶግራፎች ታሪክ ሲነበብ” በሚል ርዕስ ወመዘክርና Gerar-The Creative Hub በጋራ በመሆን የተዘጋጀው የፎቶግራፍ ዓውደ ርዕይ የካቲት 16 2016 ዓ.ም ለእይታ ክፍት ሆኗል እስከ መጋቢት 15 2016 ዓ.ም ይቆያል። የፎቶግራፍ ዓውደርዕዩ በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት አርካይቨ ውስጥ ተቀምጠው እስከዛሬ ለዕይታ ቀርበው የማያውቁ ከ200 ፎቶግራፎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ በታላላቆቹ ፎቶግራፈሮቹ ሚካኤል ፀጋዬ አና አንቶኒዮ ፍሮንቲኒ የተዘጋጀ ነው:: የፎቶግራፎ አውደርዕዩ እስኪ መጋቢት 15 2016 ዓ.ም ድረስ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል። በሌላ በኩል “የዘመን ማሚቶ” የድምፅ ቅንብር አውደርዕይ እየተካሄደ ይገኛል።ይህም አውደርዕር እስከ መጋቢት 15 2016 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል። Website: https://eventaddis.com/ Telegram: https://t.me/EventAddis1

Read More

እስማኤል መሐመድ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ እስማኤል መሐመድ ባሳለፍነው የካቲት 17 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የባላገሩ ምርጥ የፍጻሜ ውድድር ላይ ከቅዱስ ዳምጤ ጋር በእኩል ነጥብ ሶስተኛ በመውጣቱ ሽልማቱን ሳይቀበል መድረክ ጥሎ መሄዱ ይታወሳል። ይህም ክስተት በበርካታ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታታዮች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። አብዛኞቹም በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለበት ሲሉ ተደምጠዋል። ትላንትና መጋቢት 1 2016 ዓ.ም በተላለፈው ሰይፉ በኢቢኤስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረገው ቆይታ “መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ” ብሏል። በተጨማሪም እስማኤል መሐመድ በፌስቡክ ገፁ “የካቲት 17 በተካሄደው የባላገሩ ምርጥ የፍፃሜ ውድድር ላይ በዕለቱ በተሰጠኝ ደረጃ በተሰማኝን ስሜት ተከትሎ የማይገባኝን ነገር ስላደረኩኝ ዳኞችን አብርሽ ፣ ሶፊ ፤ አረጋኸን እንዲሁም የፕሮግራሙን አዘጋጆች…

Read More